አበበ ቤተ ማርያም

ግለ ታሪክ.

የቤተ ክህነት ትምህርት ደረጃ ቅዲሴ መዝገብ ቅዲሴ(፲፬ቱ ቅዲሴያት) በደብረ ዓባይ ዜማ ከነአንቀጹ በሐዋሳ ሰኣሉተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ከመ/ር አክሊለ(የቅዳሴ መምህር)
 

መዝገብ ቅዲሴ(፲፬ቱ ቅዳሴያት) በደብረ ዓባይ ዜማ ከነአንቀጹ በሐዋሳ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ከመ/ር አክሊለ(የቅዳሴ መምህር)

ምዕራፍና ጾመ ድጓ በርእሰ አድባራት ወገዲማት ዲግሚት ጽዮን አዱስ ዓለም ማርያም ከድጓ መምህሩ ከየኔታ አስተርአየ ፈንቴ ዘንድ በአግባቡ ተምሬ አጠናቅቄያለሁ።

⦁ በመጀመሪያ በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በሞረትና ጅሩ ወረዳ በደብረ ዜና ማርቆስ ገዳም ከየኔታ ስብሐት ዘንድ ክብረ በዓልና በመዝሙር ተምሬያለሁ፤

 ⦁ እንደገና ዝማሜውን በቤተ ማርያም የተክላ አቋቋም፡ ክብረ በዓልና መዝሙር(ክለሳ)፣ ወርኀ በዓል፣ መኃትው፣ (የቅኔ፣ የዝማሬና የመዋሥዕት አቋቋም)፣ እና ቅንዋት ከነእጀ ሥራው በርእሰ አድባራት ወገዲማት ዲግሚት ጽዮን አስ

ዓለም ማርያም ከመ/ር ጽጌ ወሌደ ሐናዘነድ ተምሬ አጠናቅቄያለሁ፤ በመሆኑም የአቋቋም መምህርነት የምሥክር ወረቀት ተሰጥቶኛል፤

 ⦁ ጸናጽለን ደግሞ በጎንደር በአታ ለማርያም ለዘመናዊ ትምህርት በሄድኩበት አጋጣሚ የጎንደሩን ጸናጽሌ ለሁለት ዓመት ያህል ማኅበር ቀለም ሰምቻሁ።

 ⦁ ቅኔ በመጀመሪያ በርእሰ አድባራት ወገዲማት ዲግሚት ጽዮን አዱስ ዓለም ማርያም ከየኔታ ሐዱስ ወሌደ ሐና ዘንድ በአግባቡ ተምሬ ተቀኝቻለሁ፤
⦁ በድጋሚ በምንጃርና ሸንኮራ ወረዲ በባሌጭ አማኑኤል ከየኔታ ቡሩኬ ዘንድ አጠናክሬዋለሁ።
⦁ በመጨረሻም በአዱስ አበባ ሀገረ ስብከት በፈረንሳይ አንቀጸ ምሕረት ቅደስ ሚካኤል ቤ/ክ ከየኔታ ፍሬ ስብሐት ጸጋዬ ዘንድ ቅኔ ከነአገባቡ በጥሩ ሁኔታ ተምሬ የቅኔ መምህርነት የምሥክር ወረቀት ተሰጥቶኛል።

ዝማሬ እና መዋሥዕት በደብረ ዘይት ቅደስ ሩፋኤሌ ከመ/ር ነቅአ ጥበብ ሲሻው በአግባቡ ተምሬያለሁ።

በአዱስ አበባ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮላጅ በሥነ መለኮት የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነኝ።

በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ቆይታዬ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን ለአራት ዓመታት ያህሌ በራሴ የማስተማሪያ ሞጁሌ አዘጋጅቼ ግእዝ ሳስተምር ቆይቻለሁ፤ ከዚያም በማኅበረ ቅደሳን የሐዋሳ ማዕከል ልማት ተቋማት አስተዲደር በውቅቱ ባወጣው የሥራ ማስታወቂያ ውድድር ሊይ ተሳትፌና ውድድሩን አልፌ ተቀጥሬ ለሁለት ዓመት ያህል በግእዝ መምህርነት ሠርቻለሁ።

ከዚያ በኋሊ እንደገና በአዲስ አበባ የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት ባወጣው የሥራ ማስታወቂያ ውድድር ሊይ ተሳትፌና ውድድሩን አሌፌ በሲኤምሲ ቅርንጫፍ ለስድስት ወራት ያህል የግእዝ ቋንቋን አስተምሬያለሁ።

በተጨማሪም ለአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት ለ7ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የግእዝ መማሪያ መጻሕፍትን በ2014 ዓ.ም አዘጋጅቻለሁ።

አጫጭር ሥሌጠናዎች እና ያዘጋጀኋቸውና ያሳተምኋቸው መጻሕፍት

መጻሕፍት

1. መርሀ ንባብ ወዜማ
2. ግእዝ ለሁለም ክፍሌ ፩ እና ፪
3. መዝገበ ማሕላት ዘጽጌ
4. መዝሙረ ዲዊት ንባቡ በምሌክት
ተዘጋጅተው ገና ያልታተሙ መጻሕፍት
1. መጽሐፈ ግጻዌ በልዩ አቀራረብ
2. መዝገበ ማሕላት ዘክብረ በዓል
3. መዝገበ ማሕላት ዘወርኀ በዓል
4. መዝገበ ማሕላት ዘመዝሙር
5. መዝገበ ማሕላት ዘስብሐተ ነግህ
6. ግእዝ ለሁለም ክፍሌ ፫ እና ፬
7. መጽሐፈ ቅዲሴ በልዩ አቀራረብ
8. መጽሐፈ ሰዓታት በሌል አቀራረብ

ሥሌጠናዎች

  1. በ AUTO CAD, ETABS, EAGLE POINT, እና SAP ለሦስት ወራት ሠሌጥኜ የምሥክር ወረቀት
    አግኝቻለሁ።
  2. እንደዚሁም በWATER CAD ለሦስት ወራት ሠሌጥኜ
    የምሥክር ወረቀት አግኝቻለሁ።
  3. በሌላ በኩል የቻይንኛ
    ቋንቋ ለሦስት ወራት ሠሌጥኜና ተፈትኜ ዓለም አቀፋዊ
    የምሥክር ወረቀት አግኝቻለሁ።
  4. እንደዚሁም Video Editing በቱርሚ ፊሌም አካዲሚ ሠሌጥኛሇሁ።
  5. የቤተ ክርስቲያን አገሌግልት ቀደም ሲሌ በርእሰ አድባራት ወገዲማት ዲግሚት ጽዮን
    አዱስ ዓለም ማርያም ቤተ ክርስቲያን በመዘምርነት ለስምንት ዓመት ያህል አገሌግያለሁ፤ ቀጥል በሐዋሳ  ሰዓልተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
    በአቋቋም መምህርነት አራት ዓመት ያህሌ አገሌግያለሁ። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በሰሚት በሻላ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሌደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን እያገለገሌሁ እገኛለሁ።
Shopping Cart
Scroll to Top